አሜሪካዲፕሎማሲ

ፕሬዝደንት ትራምፕ ከ5 የአፍሪካ አገራት መሪዎች ጋር ስብሰባ ሊያደርጉ ነው ተባለ፡፡

ኢትዮሞኒተር፡ 27/10/2017፡ የአሜሪካው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ከ5 የአፍሪካ አገራት ጋር ስብሰባ ሊቀመጡ መሆኑን አስታወቋል፡፡ ይህ ስብሰባ በኋይት ሀውስ የሚደረግ ሲሆን ለ2 ቀናት የሚካሄድ ነው፡፡

በሚቀጥለው ሳምንት ማለትም እ.አ.አ ከሓምሌ 9 እስከ 11 ለሚከናወነው ለዚህ ስብሰባ 5 የአፍሪካ አገራት መጥሪያ ተልኮላቸዋል፡፡

እነዚህ አገራትም ሴኔጋል፣ ጋቦን፣ ጊኒ ቢሳኦ፣ ላይቤሪያና ሞሪታኒያ ናቸው፡፡ ፕሬዝደንት ትራምፕ እንደገለፁት ከእነዚህ 5 የአፍሪካ አገራት መሪዎች ጋር የሚያደርጉት ውይይት በንግድ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ነው፡፡

አንድ አሜሪካ ባለስልጣን እንዳስታወቁት “ፕሬዝደንት ትራምፕ አሜሪካንና የአፍሪካ አጋሮቻቸውን የሚጠቅም ትልቅ የንግድ እድል በአፍሪካ ውስጥ እንዳለ እምነት ጥለዋል” ብለዋል፡፡ በዚህ በመጪው ሳምንት በሚከናወነው ስብሰባም ከ5ቱ የአፍሪካ መሪዎች ጋር በንግድና ኢንቨስትመንት ጉዳዮች ላይ ምክክር እንደሚያደርጉ ገልፀዋል፡፡
እነዚህ 5 አገራት ከአሜሪካ ጋር የንግድ ስምምነት በመፈረማቸው የተመረጡ ናቸው ተብሏል፡፡

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates