
ኢትዮሞኒተር፡ 27/10/2017፡ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በሱዳን ተፋላሚ ሃይሎች በተከበበችው ኤል ፋሸር ከተማ ሰብአዊ እረፍት እንዲያገኝ እንዲስማሙ እየጠየቀ ነው ሲሉ የመንግስታቱ ድርጅት ቃል አቀባይ ማክሰኞ ዕለት ገልጿል።
የተባበሩት መንግስታት ከፍተኛ የሰብአዊ ድርጅት ባለስልጣን ቶም ፍሌቸር ከሁለቱም የሱዳን ጦር ሃይሎች ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር ከበባው እንዲቆም ግፊት እንዲያደርጉ በዚህ ሳምንት መነጋገራቸውን ቃል አቀባዩ ስቴፋን ዱጃሪክ ተናግረዋል።
የዲፕሎማሲው ግፊት የሱዳኑ ጦር አዛዥ ጄኔራል አብደል ፋታህ አልቡርሃን ባለፈው ሳምንት ከተባበሩት መንግስታት ዋና ጸሃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ጋር ባደረጉት ጥሪ ለኤል ፋሸር የአንድ ሳምንት የእርቅ ስምምነት መስማማታቸውን ተከትሎ ነው። ሆኖም የፈጣን ድጋፍ ሰጪ ሐይሉ በዚህ ዙሪያ ምንም አይነት ምላሽ አልሰጠም።
“ከባለፈው ዓመት ሚያዝያ ጀምሮ እኛ እና አጋሮቻችን የሚያስፈልጋቸውን አስቸኳይ እርዳታ ሲቪሎች ጋር ለማድረስ የተገደበ ነበር” ሲል ዱጃሪክ ለጋዜጠኞች ተናግሯል። ጨምሮውም ውጊያው እየተባባሰ በመምጣቱ አስከፊውን የሰብአዊ ሁኔታ አጉልቶ አሳይቷል ብሏል።
ግጭቱ ከፍተኛ የሆነ የመፈናቀል ቀውስ ፈጥሯል። በኤል ፋሸር ብቻ ከሚያዝያ ወር ጀምሮ ከ400,000 በላይ ሰዎችን ከቤት ንብረታቸው እንዲፈናቀሉ ያደረገ ሲሆን በቅርቡ በሰሜን እና ምዕራብ ኮርዶፋን ግዛቶች የጸጥታ ችግር 30,000 የሚያህሉ ዜጎች መፈናቀላቸውን የአለም አቀፍ የስደተኞች ድርጅት አስታውቋል።