አሜሪካ
የቀድሞ የአሜሪካ ፕሬዝዳንቶች የUSAID እርዳታ መቆራጥን ተቃወሙ፡፡

ኢትዮሞኒተር፡ 27/10/2017፡ USAID ለተለያዩ አገራት የሚሰጠውን እርዳታ መቋረጡን ተከትሎ በአሜሪካዊያን ዘንድ ልዩነት ፈጠረ።
የአሜሪካ ዓለም አቀፍ ልማት ኤጀንሲ (USAID) ይሰጠው የነበረ እርዳታ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር በከፍተኛ እንዲቀንስ መደረጉ ይታወሳል።
ከ 80% በላይ የኤጀንሲው ፕሮግራሞች እስከ መጋቢት ወር ድረስ ተሰርዘዋል። ቀሪው ደግሞ ቀስ በቀስ እንደሚቋረጥ መረጃዎች ያሳያሉ።
በአለም ትልቁ እርዳታ ሰጪ የሆነው USAID መዘጋቱ በቀድሞ ፕሬዚዳንቶች ባራክ ኦባማ እና ጆርጅ ደብሊው ቡሽ ተወቅሷል።
በላንሴት የህክምና ጆርናል ላይ በተመራማሪዎች የታተመው ማስጠንቀቂያ እንደሚለው እነዚህ የእርዳታ ቅነሳዎች እ.ኤ.አ. በ2030 ከ14 ሚሊዮን በላይ ሰዎችን ለሞት ሊዳርጉ ይችላሉ።
ይህ ውሳኔ ሰብአዊነትን መሰረት ያላደረገ በማለት የቀድሞ ፕሮዝዳንቶች ወቅሷል።