ማህበራዊአፍሪካ

ኢትዮጵያን ጨምሮ በምስራቅ አፍሪካ ደረጃውን ያልጠበቀ የካንሰር መድሀኒት እየተሰራጨ መሆኑ አንድ ጥናት አስጠነቀቀ፡፡

ኢትዮሞኒተር፡25/10/2017፡  የድንበር ተሻጋሪ ጥናት እንዳመለከተው ኢትዮጵያ፣ ኬንያ እና ማላዊን ጨምሮ በምስራቅ አፍሪካ ሀገራት እየተሰራጩ ያሉት የኬሞቴራፒ መድሀኒቶች አለም አቀፍ የጥራት ደረጃዎችን ማሟላት ባለመቻላቸው በአካባቢው ባሉ የካንሰር ህሙማን ላይ ከፍተኛ ስጋት ፈጥሯል።

በሚያዝያ 2023 እና የካቲት 2024 መካከል በተካሄደው ዘ ላንሴት ግሎባል ሄልዝ ላይ የታተመው ጥናት በብዛት ጥቅም ላይ የሚውሉ ፀረ-ካንሰር መድሀኒቶችን ጥራት ገምግሟል፡፡ በኢትዮጵያ፣ በኬንያ፣ በማላዊ እና በካሜሩን ከሚገኙ ሆስፒታሎች እና ፋርማሲዎች 251 ናሙናዎች እንደወሰደም ጥናቱ አመላክተዋል።

በጥናቱ መሰረት የላቦራቶሪ ትንታኔ እንደሚያሳየው የመድኃኒት ንጥረ ነገር መጠን ከ28% እስከ 120 በመቶው ከተገለጸው ይዘት ውስጥ ነው። የመድኃኒቶቹ ውድቀት ከ 14% ወደ 24% ሲሆን በአራቱ አገሮች መካከል ምንም ልዩነት የለም ብለዋል፡፡

በአጠቃላይ ከ251 ናሙናዎች (24%) 59 የሚሆኑት በምርመራ ወቅት የአገልግሎት ጊዜያቸው ያለፈባቸው ሲሆን የተወሰኑት ደግሞ እስከ አንድ አመት የሚደርሱ ናቸው ሲል ጥናቱ አመልክቷል።

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates