ኢትዮጵያኢኮኖሚ

ሳፋሪኮም ከ7 ሚሊዮን የኢንተርኔት ተጠቃሚ ኢትዮጵዊያን ደንበኞች ማፍራቱን ኣስታወቀ፡፡

ኢትዮሞኒተር፡25/10/2017፡ “በየወሩ በአማካኝ ስድስት ነጥብ አምስት ጌጋ ባይት የኢንተርኔት ተጠቃሚ ከሰባት ሚሊየን በላይ ኢትዮጵያውያን ደንበኞች አፍርቻለሁ” ሲል ሳፋሪኮም አስታውቀዋል፡፡

በኢትዮጵያ የቴሎኮም ገበያ ከተሰማራ አራት አመት ያልሞላው ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የደንበኞቹ ቁጥር 10 ሚሊየን መድረሱን አስታውቃዋል፡፡ በመላ ሀገሪቱ ለ90 ቀናት የዕለት ተዕለት የስልክ አገልግሎታቸው ሳፋሪኮም የቴሌኮም አገልግሎት የተጠቀሙ 10 ሚሊየን ደንበኞች አፍርቻለሁ ሲል ገልጿል።

ከ10 ሚሊየን ደንበኞቼ ውስጥ ሰባት ነጥብ አንድ ሚሊየን የሚሆኑት የኢንተርኔት አገልግሎቴን ይጠቀማሉ ያለው ሳፋሪኮም በአማካኝ እያንዳንዱ ደንበኛየ በወር ስድስት ነጥብ አምስት ጌጋ ባይት ይጠቀማል ሲል ገልፀዋል።

ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ላለፉት አራት አመት ለሚጠጋ ጊዜው በአጠቃላይ 300 ቢሊየን ብር ኢንቨስት ማድረጉን ጠቁሟል።

ተቋሙ በኢትዮጵያ በ150 ከተሞች እየሰጠው በሚገኘው አራተኛው ትውልድ (4ጂ) የኢንተርኔት አገልግሎት በየቀኑ 31 ሺህ አዳዲስ ደንበኞች እየተቀላቀሉኝ ነው ብሏል።

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates