
ኢትዮሞኒተር፡25/10/2017፡ በአብዲራህማን መሃዲ የሚመራው የኦጋዴን ብሔራዊ ነጻነት ግንባር (ኦብነግ) ባሳለፍነው ሳምንት ሌላኛው የፓርቲው አንጃ በጅግጅጋ ያካሄደውን ጉባኤ “ህገወጥ፣ በፖለቲካ የተቀነባበረ እና ሀሰተኛ ጉባኤ ነው” ሲል ተቃወሞታል።
ፓርቲው ይህን ያለው፤ ባሳለፍነው ሳምንት መገባደጃ ሰኔ 22 ቀን 2017 ዓ.ም የኦብነግ አንደኛው ቡድን የፓርቲውን 5ኛ መደበኛ ጉባኤ በማካሄድ አብዲራህማን ማህዲንን ከሊቀመንበርነት ማንሳቱን ተከትሎ ነው።
በጅግጅጋ የተካሄደው ጉባኤ “በብልጽግና ፓርቲ አስተባባሪነት፣ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ እና በሶማሌ ክልል አስተዳደር ድጋፍ የተደረገ ነው” ያለው በአብዲራህማን መሃዲ የሚመራው ኦብነግ መግለጫው፤ “ፓርቲውን ለማፍረስ፣ የኦጋዴንን የተፈጥሮ ሀብት ለመበዝበዝ እና የሶማሌ ሕዝብ በህገመንግስቱ የተሰጠውን ራሱን የማስተዳደር መብት ለመሸርሸር” የሚደረገው ሰፊ ጥረት አካል ነው ሲል ከሷል።