
ኢትዮሞኒተር፡25/10/2017፡ በትግረይ ክልል ከሚመረተው ወርቅ በየዓመቱ እስከ 80 ሚሊዪን ዶላር የሚያወጣ ወርቅ በሕገ ወጥ መንገድ ወደ ኤርትራ እንደሚወጣ ሪፖርቱ ያሳያል፡፡
ዘ ሴንትሪ የተሰኘው ድርጅት ሪፖርት እንደሚያሳየው በትግረይ ክልል የሚደረገው የወርቅ ፍለጋ ውድድር የሌለበትና ውስብስብ ነው ብሎታል፡፡ ከክልሉ መአድንና ኢነርጂ ቢሮ የወጣው መረጃ እንደሚመለክተው ከሆነ በየዓመቱ ከሚመረተው ወርቅ ከ75 እስከ 80 ሚሊዮን ዶላር የሚገመት በጥቁር ገበያ አማከኝነት ይወጣል፡፡
የኤርትራ ሰራዊት በሚቆጣጠርባቸው የትግራይ ግዛቶች ሳይቀር ወታደሮቹ የቀን ሰራተኞች በማሰማራት ከ20 እስከ 30 በመቶ ክፍያ እንደሚከፍሉ ሪፖርቱ ጠቁመዋል፡፡
በተለይ በሰሜናዊ ምዕራብ ዞን በሚገኙ አከባቢዎች ከፍተኛ ሕገ ወጥ የወርቅ ቁፋሮ የሚደረግባቸው እንደሆኑ የገለፀው ዘ ሴንትሪ ሽረ ደግሞ ዋነና ሕገ ወጥ የወርቅ ንግድ ልውውጥ የሚደረግባት ከተማ መሆንዋ ጠቅሰዋል፡፡