መካከለኛ ምስራቅ
እስራኤል ለ60 ቀናት በጋዛ የተኩስ አቁም ለማድረግ መስማማቷን ትራምፕ አስታወቁ!

ኢትዮሞኒተር፡25/10/2017፡ የአሜሪካው ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ እስራኤል በጋዛ የ60 ቀናት የተኩስ አቁም ስምምነትን ለማድረግ “አስፈላጊ ቅድመ ሁኔታዎችን” ለማሟላት ተስማምታለች ሲሉ ተናገረዋል።
ፕሬዚደንቱ በትሩዝ የማኅበራዊ ሚዲያቸው ላይ እንደጻፉት ከሆነ በምክረ ሃሳቡ ስምምነት ወቅት “ጦርነቱን ለማቆም ከሁሉም አካላት ጋር እንሰራለን” ብለዋል፡፡ “ሰላም ለማምጣት በጣም ጠንክረው የሠሩት ኳታራውያን እና ግብፃውያን የመጨረሻውን ምክረ ሀሳብ ያቀርባሉ።
ሃማስ ይህንን ስምምነት ይቀበላል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ። ምክንያቱም የተሻለ አይሆንም፤ እየባሰ ነው የሚሄደው” ሲሉ ትራምፕ ጽፈዋል። መስከረም 26/2016 ዓ.ም. ሃማስ በእስራኤል ላይ ድንገተኛ ጥቀቃት ከፈፀመ ጀምሮ ቢያንስ 56,647 ፍልስጤማውያን ተገድለዋል።