
ኢትዮሞኒተር፡25/10/2017፡ ከዋናዉ የአውሮፓ ምድር የእንግሊዝ የባሕር ቦይን አቋርጠዉ ወደ ታላቋ ብሪታንያ የገቡ ስደተኞች ቁጥር ወደ 20,000 እንደሚጠጋ የሐገሪቱ ባለስልጣናት ገልፀዋል።
በስድት ወር ዉስጥ ይህን ያህል ሰዉ ወደ ብሪታኒያ ሲገባ ያሁኑ ከፍተኛዉ ነዉ ተብሏል። በዘገባዉ መሰረት ስደተኞቹ ባህሩን የተሻገሩት በአነስተኛና ደረጃቸውን ባልጠበቁ ጀልባዎች ለሕይወታቸው አደገኛ በሆነ መልኩ ነዉ።
እ.አ.አ በ2024 ግማሽ ዓመት ባሕሩን አቋርጠዉ ብሪታንያ የገቡት ስደተኞች ቁጥር ወደ 13,500 የሚጠጋ የነበረ ሲሆን በያዝነው ዓመት አጋማሽ ግን ወደ 20,000 ገደማ ተጠግቷል። በአንድ ቀን ብቻ 879 ስደተኞች መሻገራቸውን የገለጸው የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት በአመቱ በአንድ ቀን የገቡ ስደተኞች ከፍተኛውን ቁጥር እንደሆነ አክሏል።