ኢትዮጵያፖለቲካ

በኢትዮጵያ ባለፉት 15 ቀናት ብቻ 89 ሰዎች መሞታቸው ተገለፀ፡፡

ኢትዮሞኒተር፡ 20/10/2017፡ ኢትዮጵያን ፒስ ኦብዘርቫቶሪ ባወጣው አዲስ ሪፖርት ባለፉት 15 ቀናት በኢትዮጵያ ውስጥ 38 ፖለቲካዊ ግጭቶች መከሰታቸውን ያሳያል፡፡

በሪፖርቱ ይህ ቀደም ካለው ሁለት ሳምንት ጋር ሲነፃፀር በ28 በመቶ ቀንሶ መገኘቱን ጠቅሶ በእነዚህ ቀናት በሰላማዊ ሰዎች ላይ ያነጣጠሩ 14 ጥቃቶች መደረጋቸውን አስረድቷል፡፡ በሰላማዊ ሰዎች ላይ የተፈፀሙት እነዚህ ጥቃቶች ቀደም ካለው 15 ቀናት ጋር ሲነፃፀር በ21 በመቶ መጨመሩን አስታውቋል፡፡

ባለፉት ሁለት ሳምንታት በተከሰቱት ፖለቲካዊ ግጭቶች ህይወታቸው ያለፈው ሰዎች 89 መሆናቸውን የጠቀሰው ሪፖርቱ ይህ ቀደም ካለው ሁለት ሳምንት ጋር ሲነፃፀር በ59 በመቶ እንደቀነሰ ገልጿል፡፡

ኢትዮጵያ ፒስ ኦቭዘርባቶሪ (epo) የኢትዮጵያ ጋምቤላ ክልል ባለፉት ሁለት ሳምንታት በድንበር ተሻጋሪ ወታደራዊ ግጭቶች እና በውስጥ ጥቃቶች እየታመሰ ነው ብለዋል። በክልሉ በኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት እና በደቡብ ሱዳን ህዝባዊ መከላከያ ሠራዊት (SSPDF) መካከል በተቀሰቀሰ ግጭት የሰው ህይወት ጠፍቷል፤ በርካቶችም ተፈናቅለዋል ነው ያለው ሪፖርቱ።

ግጭቱ የተቀሰቀሰው ከኢትዮጵያ ወደ ደቡብ ሱዳን ስትጓዝ የነበረች ጀልባ ደቡብ ሱዳን ህዝባዊ መከላከያ ሠራዊት ወታደሮች ተኩስ ከተከፈተባት በኋላ ነው። ይህንን ተከትሎ በሁለቱ ሀገራት ኃይሎች መካከል የከባድ መሳሪያ ልውውጥ የተደረገ ሲሆን ይህም በድንበር አካባቢ በሚኖሩ ሲቪሎች ላይ ከፍተኛ መፈናቀልን አስከትሏል።

ትላንት በወጣው ሪፖርት መሠረት, ከሰኔ 7 እስከ 20 ባለው ጊዜ ውስጥ በኢታንግ ልዩ ወረዳ እና በአግኑዋክ ዞን ቢያንስ ሶስት የተለያዩ ጥቃቶች በሰላማዊ ሰዎች ላይ እና በፖሊስ ጣቢያ ላይ፣ አንድ ጥቃት በኢታንግ ልዩ ወረዳ እና በአግኑዋክ ዞን ስምንት ሰዎች መሞታቸው መመዝገባቸው አመላክተዋል። ሰኔ 9 ቀን የፖሊስ አባልን ጨምሮ ማንነታቸው ያልታወቁ የታጠቁ ተዋናዮች በኢታንግ ከተማ በሚገኘው ፖሊስ ጣቢያ ላይ ጥቃት ሰንዝረዋል ።

የድንበሩ ውጥረት በደቡብ ሱዳን ካለው የውስጥ የፖለቲካ አለመረጋጋት ጋር በቀጥታ የተያያዘ እንደሆነም ተገልፀዋል።

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates