
ኢትዮሞኒተር፡ 19/10/2017፡ የሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃል ኪዳን ድርጅት (ኔቶ) አባል ሃገራት ከጠቅላላ የሀገር ውስጥ ምርታቸዉ 5 በመቶውን ለማዋጣት ተስማሙ።
የሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃል ኪዳን ድርጅት (ኔቶ) አባል ሃገራት መሪዎች ከፍተኛ የመከላከያ ወጪን ለመገንባት ከጠቅላላ የሀገር ውስጥ ምርታቸዉ 5 በመቶውን ለማዋጣት ተስማሙ። አባላቱ የትኛውም አባል ሀገራት ጥቃት በሚደርስበት ጊዜ ለጋራ መከላከያ ኔቶ የጋራ ደህንነት ዋስትናን ለመስጠት “ጠንካራ ቁርጠኝነት” እንዳላቸዉ አጽንኦት ሰጥተዋል። በኔዘርላንድስ ዴንሃግ በተካሄደዉ የኔቶ አባል ሃገራት ጉባኤ ላይ አባል ሃገራቱ ከጠቅላላ የሃገር ዉስጥ ምርታቸዉ 5 በመቶውን ለማዋጣት የተስማሙት፤ የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዝዳንት የዶናልድ ትራምፕን ጥያቄ ተከትሎ ቢሆንም አውሮጳውያኑ ላይ ከሩሲያ የሚታየዉ ፀጥታ ስጋት እየጨመረ መሆኑን የሚያንፀባርቅ ነው ። የኔቶ አጋሮችም ሩሲያ ለአውሮፓ አትላንቲክ ደህንነት የረዥም ጊዜ ስጋት መሆኗን በማወጅ ለዩክሬን ድጋፏቸዉን እንደሚቀጥሉ ቃል ገብተዋል። ስለዚህም አውሮጳ እና ካናዳ ለኔቶ የበለጠ አስተዋፅኦ ማበርከት አለባቸው ሲሉ የኔቶ ዋና ፀሐፊ ማርክ ሩት ተናግረዋል። የመከላከያ አቅማቸዉን የሚያሳድጉ አባላት ህብረቱ ሩሲያን ጨምሮ ከማንኛውም በኩል የሚመጣን ስጋት መከላከል ያስችላቸዋል ሲሉ አክለዋል። ይህ በንዲህ እንዳለ የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ዩናይትድ ስቴትስ የታሪፍ ገደቦችን እንድትቀንስ ጥሪ አቅርበዋል ፣ በኔቶ አጋሮች መካከል የሚደረገውን የንግድ ጦርነት “ውዥንብር” ብለውታል።