አፍሪካፖለቲካ

”የኮታ ፖለቲካ አይሰራም” ጠቅላይ ሚኒስትሩ

ኢትዮ ሞኒተር፡ 13/10/2017፡ የሱዳን ጠቅላይ ሚኒስትር “የተስፋ መንግሥት” ያሉትን አደረጃጀት ይፋ አደረጉ። ከዚህ በፊት የነበረው የፖለቲካ ኮታ ውድቅ አድርጎታል።

የሱዳን አዲስ ጠቅላይ ሚኒስትር ካሚል ኢድሪስ ሐሙስ ዕለት ከፓርቲ ውጪ የሆነ  የመንግስት መዋቅር ማቀዳቸው አስታውቀዋል። ይህ እርምጃ ከሠራዊቱ ጋር በመተባበር ከታጠቁ ቡድኖች ጋር ያለውን የስልጣን ክፍፍል በቀጥታ የሚፈታተን እርምጃ ነው ተብሏል።

እ.ኤ.አ. በግንቦት 19 በጦር ኃይሎች አዛዥ ጄነራል አብዱልፈታህ አልቡርሃን የተሾሙ ካሚል ኢድሪስ እ.ኤ.አ. በ2021 ወታደራዊ መፈንቅለ መንግስት ተከትሎ አብደላ ሀምዶክ ከስልጣን ከለቀቁ በኋላ የመጀመርያው ሰው ናቸው።

ከገለልተኛ ባለሙያዎች የተውጣጣው 22 አባላት ላሉት “የተስፋ መንግሥት” ያሉት እቅድ የ2020 የጁባ የሰላም ስምምነትን በቀጥታ ይጋፋል በማለት ትችት ገጥሞታል። በዚህ ስምምነት መሰረት የፍትህ እና የእኩልነት ንቅናቄ መሪ የሆኑት ጂብሪል ኢብራሂም የፋይናንስ ሚኒስትር ሲሆኑ በሚኒ ሚናዊ የሚመራው የሱዳን ነፃ አውጪ ንቅናቄ ተወካይ ደግሞ የማዕድን ሚኒስቴርን ለማድረግ መታቀዱ መረጃዎች አሳይቷል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኢድሪስ በአገሪቱ ቴሌቪዥን በተላለፈው ንግግራቸው የፖለቲካ ኮታዎችን እና ዘመድ አዝማድነትን በሁሉም መልኩ ከመንግስት መዝገበ ቃላት እንደሚሰርዝ ተናግሯል። አላማው “በጣም ብቁ፣ ልምድ ያለው እና በመልካም ስም እና ታማኝነት ላይ የተመሰረተ ፍትሃዊ ሹመቶችን ማሳካት እንደሆነም ተናግሯል።

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates