አሜሪካፖለቲካ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ከአሜሪካው ማሪን ኮርፕስ ጄነራልና የአፍሪኮም አዛዥ ጋር መወያየታቸው ተገለፀ።

ኢትዮ ሞኒተር፡ 13/10/2017፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከአሜሪካ ማሪን ኮርፕስ ጄነራልና የአፍሪኮም አዛዥ ከሆኑት ጄነራል ማይክል ላንግሌይ ጋር በዛሬው ዕለት ተወያይተዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ የትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት፥ የጋራ ፍላጎት በሆኑ የሁለትዮሽና ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ ከጄነራል ማይክል ላንግሌይ ጋር ውይይት አድርገናል ብለዋል።
የአሜሪካ አፍሪካ ኮማንድ (AFRICOM) አዛዥ ጄኔራል ሚካኤል ላንግሌይ ኢትዮጵያን ጎብኝተው ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ጋር ተገናኝተዋል።
ውይይታቸውም በአፍሪካ ቀንድ የአልሸባብ እና የአይኤስ የሽብር ስጋትን ለመከላከል ላይ ያተኮረ እንደነበር ገልጿል።

የጄኔራል ሚካኤል ላንግሌይ የኢትዮጵያ ጉብኝት የአሜሪካ የልዑካን ቡድንን ትላንት በሶማሌላንድ የነበረው ቆይታ ካጠናቀቀ በኃላ የተደረገ ነው።

የሶማሊላንዶ ፕሬዝዳንት ፅህፈት ቤት ባወጣው መግለጫ “ይህ ጉብኝት የሁለትዮሽ የመከላከያ፣ የንግድ እና የጸጥታ ትብብርን ለማጠናከር ያለንን የጋራ ቁርጠኝነት ያሳያል” ብሏል።

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates