
ኢትዮ ሞኒተር፡ 13/10/2017፡ ኢትዮጵያ በኑሮ ውድነት ከአፍሪካ አገሮች ቀዳሚ ደረጃ መያዟን አንድ ሪፖርት አመለከተ።
ኢትዮጵያ ለመኖር እጅግ ውድ ከሆኑ የአፍሪካ ሀገሮች መካከል ቀዳሚ ደረጃ ስትይዝ ከዓለም 53ኛ ደረጃ ላይ መቀመጧን ሪፖርቱ አመላከቷል።
የዓለማችን ትልቁ የኑሮ ውድነት የመረጃ ቋት ባወጣው አዲስ ሪፖርት እንዳስታወቀው፤ ኢትዮጵያውያን አሁን ላይ እንደ ምግብ እና ትራንስፖርት ባሉ መሰረታዊ ነገሮች ላይ ከሌሎች የአፍሪካ ሀገሮች ዜጎች የበለጠ ገንዘባቸውን ያወጣሉ።
በሪፖርቱ መሰረት፣ በኑሮ ውድነት ኢትዮጵያ ከዓለም 53ኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠችው 46.5 የኑሮ ውድነት ጠቋሚ ነጥብ በመስመዝገብ ሲሆን፣ ይህም አፍሪካ ውስጥ ካሉ አገሮች ሁሉ ከፍተኛው ነው ተብሏል።
በሀገሪቱ የሚታየው የሸቀጦች ዋጋ መወደድ በኑሮ ውድነት ደረጃ አንደኛ እንድትሆን ምክንያት መሆኑም ሪፖርቱ አመልክቷል። ይህም በተለይ በቋሚ ወይም በዝቅተኛ ገቢ የሚኖሩ ሰዎች ሳምንታዊ ወጪያቸውን ለመሸፈን እየከበዳቸው መምጣቱን የወጣው ሪፖርት ጠቁሟል።