
ኢትዮ ሞኒተር፡ 11/10/2017፡ ምርጫ ቦርዱ ለጊዝያዊ አስተዳደሩ በፃፈው ደብዳቤ ፓርቲው በትግራይ ክልል ውስጥ በሁሉም ዞኖች፣ ወረዳዎች፣ ከተሞችና ቀበሌዎች ተንቀሳቅሶ አባላትን ለመመልመል እንዲችል ለክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር የትብብር ደብዳቤ እንዲፃፍለት ጥያቅ ማቅረቡን ጠቅሷል፡፡
የምርጫ ቦርድ ደብዳቤ “በመሆኑም የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተረዳደር የዲሞክራሲያዊ ስምረት ትግራይ(ስምረት) መስራቾች ፓርቲውን ለማስመዝገብ የሚያስፈልጉ ተግባራትን ለማከናወን ይረዳቸው ዘንድ በትግራይ ክልል ለሚያደርጉት እንቅስቃሴ አስፈላጊው ትብብር እንዲደረግላቸው በአክብሮት እናሳስባለን” ብሏል፡፡
ከህወሓት ከወጡ በእነ ጌታቸው ረዳ የተቋቋመው ስምረት የፖለቲካ ፓርቲ ለመሆን ላቀረበው ጥያቄ ግንቦት 18 ቀን 2017 ከምርጫ ቦርድ ጊዜያዊ የምዝገባ ፈቃድ እንደተሰጠው ይታወሳል፡፡