ማህበራዊ

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት “መርማሪዎችን በወንጀል የማይጠየቁበት አዋጅ አፀደቀ።

አዋጁ በፓርላማ አባላትና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ተቃውሞ ገጥሞታል።

ኢትዮ ሞኒተር፡ 11/10/2017፡ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በወንጀል የተገኘ ንብረት ሕጋዊ ማስመሰል እና ሽብርተኝነትን በገንዘብ መርዳት ወንጀልን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የቀረበውን ረቂቅ አዋጅ በ3 ተቃውሞና በ1 ድምፀ ተዐቅቦ በአብላጫ ድምፅ አፅድቆታል። በዚህ ዐዋጅ መሠረት መሰል ወንጀሎችን ለመመርመር የተመደበ ሰው በሥራ  ላይ እያለ “ከግድያ ወንጀል በስተቀር ለሚፈጽመው የወንጀል ድርጊት የወንጀል ክስ አይቀርብበትም” በሚል መደንገጉ ጥያቄ አስነስቷል። ይህ ድንጋጌ በምርመራ ሽፋን የመንግሥት ተቃዋሚዎችን፣ የመብት ተሟጋቾችን፣ ጋዜጠኞችን እና ነጋዴዎችን ለማጥቃት የተረቀቀ እና የዜጎችን መብት የሚጎዳ ነው የሚል ከፓርላማ ኣባላት ተቃውሞ ገጥሞታል።
አዋጁን ያዘጋጁት አካላት ግን የሕጉ መንፈስ ይህ አለመሆኑን ጠቅሰው አላማው ሽብርተኝነትን መከላከል ነው ብለዋል።
ይሁን እንጂ ከዚህ በፊት ከነበረው የሽብርተኝነት ወንጀል አዋጅ በላይ ሰብአዊ መብቶች የሚገድብና መርማሪዎች የሰው ልጆች ላይ እንደፈለጉ እንድያደርጉ የሚፈቅድ ነው የሚል ስጋት ፈጥሯል። ከዚህ በተጨማሪ “መርማሪዎች ከሞት በስተቀር ወንጀል ቢፈፅሙ እንኳን አይጠየቁም” የሚለውን ዓረፍተ ነገር “ወንጀል መፈፀሙ እየታወቀ በየተኛው ዓለም ነው የማይጠየቀው?” በሚል ትችት እየደረሰበት ነው።

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates