ማህበራዊኢትዮጵያ

በትግራይ ክልል ከ480 በላይ የጅምላ መቃብሮች እንደተገኙ ተገለፀ።

ኢትዮ ሞኒተር፡ 09/10/2017፡ የክልሉ የዘር ማጥፋት ጥናት ኮሚሽን ዛሬ ሰኔ 9 ቀን 2017 ዓ/ም እንዳስታወቀው በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ የመሰረተ ልማት ውድመት እና ከ690,000 በላይ አባወራዎች ጥናት አድርጓል።

ኮሚሽኑ ይህንን ያስታወቀው ክልላዊ የምክክር መድረክ ዛሬ በመቀሌ ባደረገበት ወቅት ነው።

የትግራይ የዘር ማጥፋት ጥናት ኮሚሽን ኮሚሽነር ረዳት ፕሮፌሰር የማነ ዘርዓይ እንዳሉት በትግራይ የደረሰውን የሰው ህይወት፣ ንብረትና የተፈጥሮ ሃብት ውድመት በሰነድ መመዝገብ አለበት።

ኮሚሽነር የማነ በትግራይ የተፈፀመው የዘር ማጥፋት ወንጀል በሰው ልጆች ላይ የተፈፀመ ዘግናኝ ተግባር ነው ብለዋል። ኮሚሽኑ ከ480 በላይ የጅምላ መቃብሮችን መዝግቦ መያዙን እና በ693,872 ቤተሰቦች ላይ ትክክለኛ መረጃ መሰነዱን ጠቁመዋል።

ኮሚሽነሩ በመሰረታዊ አገልግሎቶች ማለትም በትምህርት፣ በጤና እና በሌሎች ላይ የደረሰው ጉዳት ከፍተኛ መሆኑን ተናግረዋል። በትግራይ ያለው የድህነት መጠን በ2007 ከነበረበት 29 ነጥብ 6 በመቶ በ2014 91 በመቶ ደርሷል ብለዋል።

በአንድ ወረዳ ከተደፈሩት 210 ሴቶች መካከል 57ቱ ኤች አይ ቪ ኤድስ በደማቸው ውስጥ መገኘቱም ኮሚሽኑ አስታውቋል።

ኮሚሽኑ እንዳስታወቀው ጥናቱ በወራሪ ሐይሎች ስር የሚገኙ የትግራይ ግዛቶች አያጠቃልልም።
በመድረኩ የተገኙት የትግራይ ጊዝያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ጄነራል ታደሰ ወረደ መረጃው መሰብሰቡ ለፍትህና ተጠያቂነት ወሳኝ መሆኑ ገልጿል።

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates