ፖለቲካ

“ኢራን ለእስራኤል የምትሰጠውን ግብረ መልስ ልታቁም እንደምትችል አስታወቀች::

ኢትዮ ሞኒተር፡ 09/10/2017፡ የኢራን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እንደገለፀው “እስራኤል ጥቃቷን ካቆመች የእኛ ምላሽም ይቆማል” ብሏል፡፡

የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራግቺ በትላንትናው እለት በቴሄራን ለሚገኙ ዲፕሎማቶች በሰጡት መግለጫ “እኛ ራሳችንን እየተከላከልን ነው፡፡ የእኛ ራስን መከላከል ደግሞ ህጋዊ መሰረት ያለው ነው፡፡ ለተቃጣብን ጥቃት የምናደርገው ምላሽ ነው፡፡ ጥቃቱ ከቆመ የእኛ ምላሽም እናቁማለን” ብለዋል፡፡

ሚኒስትሩ በተጨማሪ “እስራኤል በደቡባዊ ፓርስ የነዳጅ ማውጫ ላይ የፈፀመችው ጥቃት ትልቅ ስህተት ነው፡፡ ይህ የነዳጅ ማውጫ እኛና ኳታር በጋራ የምናስተዳድረው ነው፡፡ እስራኤል ግጭቱን ከኢራን ግዛት ውጭም የማስፋፋት አላማ እንዳላት ይህ ማሳያ ነው” በማለት እስራኤል ኮታርም ጭምር እየነካች እንደሆነች ተናግሯል፡፡ በአሜሪካና ኢራን መካከል እየተካሄደ ያለውን የኒውክሌይር ድርድር እስራኤል ሆነ ብላ ለማሰናከል የጀመረችው ግጭት መሆኑን የጠቀሱት ሚኒስትሩ ጨምረውም የእስራኤል ጥቃት ካለአሜሪካ እውቅና እንደማይደረግ ገልፀዋል፡፡

“በጥቃቱ ላይ አሜሪካ ምንም ተሳትፎ እንዳላደረገች በተለያዩ መንገዶች መልእክቶች እየደረሱን ነው፡፡  ነገር ግን እኛ ይህንን አናምንም፡፡ እንደውም በዚህ ጉዳይ ላይ ማስረጃዎችን እያሰባሰብን ነው” በማለት መግለፃቸውን ዘገባዎች አመላክቷል፡፡

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates