ኢኮኖሚ
በአማራ ክልል ጎንደር አከባቢ ሄሊኮፕተር መውደቋ ተገለፀ።

ኢትዮ ሞኒተር፡ 09/10/2017፡ የአማራ ሚድያ ኮርፖሬሽን የክልሉ የኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ጠቅሶ እንዘገበው ሄሊኮፕተሩ በቴክኒክ ምክንያት ነው የተባላሸው ብለዋል፡፡
በሄሊኮፕቶሯ ውስጥ ከነበሩት የፌደራል መንግስት ባለስልጣናት የኢፌዲሪ ፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀስላሴ፣ ም/ል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተመስገን ጥሩነህ፣ የክልሉ ርእሰ መስተዳደር ከበደ አረጋና ሌሎች ባለስልጣናት እንደነበሩ ተገልጿል።
የፌደራል መንግስት የሄሊኮፕተሯ መውደቅ ምክንያት በይፋ ባይገልፅ የአማራ ክልል መንግስት ግን የቴክኒክ ብልሽት መሆኑና የተጎዳ ሰው እንደሌለ አስታወቀች ቋል።
ይሁን እንጂ የአማራ ፋኖ ሄሊኮፕተሯን መትቶ እንደጣላት እየገለፀ ነው።
የአማራ ፋኖ ከፍተኛ የፌደራል ባለስልጣናት ጭና ወደ ጎንደር ስትጓዝ የነበረች ሄሊኮፕተር መትቶ ጎርጎራ አከባቢ እንደጣላት ገልጿል።
በውጭ አገር የሚገኙ የፋኖ ደጋፊ ሚድያዎችም ሄሊኮፕተር ጣለን በማለት ሰበር ዜና እያስነገሩ ነው።
ቢሆን ከመንግስት አካላት እስካሁን ተጨማሪ መረጃዎች አልወጡም።