ኢኮኖሚ
የድፍድፍ ነዳጅ ዋጋ 13 በመቶ ጭማሪ ማሳየቱን ተገለፀ፡፡

ኢትዮ ሞኒተር፡ 06/10/2017: እስራኤል ኢራን ላይ ከፍተኛ የአየር ጥቃት ከሰነዘረች በኋላ የድፍድፍ ነዳጅ ዋጋ 13 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል።
ከ2020 በኋላ በቀን ውስጥ በዚህ ደረጃ ሲጨምር ከፍተኛው ነው ተብሏል።
የአንድ በርሜል የብሬንት ድፍድፍ ነዳጅ ዋጋ 78 ዶላር ገብቷል።
አሁን ያለው ውጥረት በመካከለኛው ምስራቅ ያለውን የአቅርቦት ሰንሰለት ላይ መቆራረጥ እንዳይፈጥር ተሰግቷል።
ተንታኞች ውጥረቱ ተባብሶ በዚሁ ከቀጠለ ሁኔታው የዓለምን የኃይል ገበያ የበለጠ ሊያናጋ እንደሚችል አስጠንቅቀዋል።
ኢራን በቀን እስከ 3.3 ሚሊዮን በርሜል ታወጣለች፣ ይህም ከዓለም አቀፍ አቅርቦት 3 በመቶውን ይሸፍናል።