ኢትዮጵያኢኮኖሚ

ከኢትዮጵያ የ2018 አጠቃላይ በጀት 24 በመቶ ገደማ ለዕዳ ክፍያ የተመደበ ነው ተባለ።

ኢትዮ ሞኒተር: 05/10/2017: ከ2018 የኢትዮጵያ 1.93 ትሪሊዮን ብር በጀት 463 ቢሊዮን ብር ለዕዳ ክፍያ መመደቡ የገንዘብ ሚኒስቴር አስታውቋል። የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት “የተሟላ” የሚሉት የኢኮኖሚ ማሻሻያ ላይ ያተኮረው በጀት ለአዳዲስ ፕሮጀክቶች ገንዘብ አልመመመደቡም ታውቋል።

የኢትዮጵያ መንግስት ለ2018 ካዘጋጀው 1.93 ትሪሊዮን ብር በጀት 463 ቢሊዮን ብር ለዕዳ ክፍያ እንዲውል መድቧል። “ለሀገር ውስጥ እና ለውጭ ሀገር” ዕዳ ክፍያ የተደለደለው የገንዘብ መጠን ከአጠቃላይ የ2018 በጀት 24 በመቶ ገደማ፤ ከመንግስት የመደበኛ ወጪ 39 በመቶ  ድርሻ አለው ተብሏል።


ለ2018 የተዘጋጀው በጀት ከተያዘው ዓመት ጋር በ494 ቢሊዮን ብር ጨምሯል። ይህ ከ2017 መደበኛ እና ተጨማሪ በጀት 34.4 በመቶ ዕድገት ያለው ሲሆን በ2018 በጀት ለፌድራል መንግሥት መደበኛ ወጪ 1.8 ትሪሊዮን ብር፤ ለካፒታል ወጪ በአንጻሩ 415 ቢሊዮን ብር ገደማ ተመድቧል። ከሚቀጥለው ዓመት በጀት የክልሎች ድጋፍ 315 ቢሊዮን ብር ድርሻ ሲኖረው ለዘላቂ የልማት ግቦች ማስፈጸሚያ 14 ቢሊዮን ብር ተመድቧል።
የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አሕመድ ሽዴ “የመደበኛ በጀቱን ያሳበጠው” ለዕዳ ክፍያ የተመደበው እንደሆነ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት አስረድተዋል።

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates