ማህበራዊ

በዓለም አቀፍ ደረጃ በጦርነት እና ግጭት የተፈናቀሉ ዜጎች 122 ሚሊዮን መድረሱን የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ድርጅት አስታወቀ።

ኢትዮ ሞኒተር: 05/10/2017: በሱዳን እና ዩክሬን ባሉ የረጅም ጊዜ ግጭቶች ሳቢያ በአለም ላይ በጦርነት እና በስደት የተፈናቀሉ ሰዎች ቁጥር ከ122 ሚሊዮን በላይ ሆኖ ቆይቷል ሲል የመንግስታቱ ድርጅት የስደተኞች ኤጀንሲ ዛሬ አስታወቀ።

በአለም አቀፍ ደረጃ ከመኖሪያ ቤታቸው በግዳጅ የተፈናቀሉ ሰዎች ቁጥር ከተመዘገበው ከፍተኛ በመጠኑ ቢቀንስም “አሁንም ከፍተኛ ነው” ሲል የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ገልጿል።

እ.ኤ.አ. በ2024 መጨረሻ በዓለም ዙሪያ 123.2 ሚሊዮን ሰዎች ከቤት ንብረታቸው በግዳጅ መፈናቀላቸውን የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ኤጀንሲ/UNHR አስታውቋል።

ነገር ግን ይህ አሃዝ በዚህ አመት በሚያዝያ ወር መጨረሻ ወደ 122.1 ሚሊዮን ዝቅ ማለቱን የጠቀሰው የኤጀንሲው ሪፖርት፣ ይህም ሶሪያውያን ከብዙ አመታት ብጥብጥ በኋላ ወደ አገራቸው መመለስ በመጀመራቸው ነው ብሏል።

ወደ ሁለት ሚሊዮን የሚጠጉ ሶሪያውያን ከውጪ ወደ አገራቸው መመለስ መቻላቸውም ሪፖርቱ አመልክቷል።

ነገር ግን ኤጀንሲው አስጠንቅቋል፤ በአለም አቀፍ ደረጃ ታላላቅ ግጭቶች ከተከሰቱ አሃዙ እንደገና ሊጨምር እንደሚችል ስጋቱ ገልጿል።

ኤጀንሲው እንዳለው በአለም አቀፍ ደረጃ በጦርነት፣ በአመጽ እና በስደት የተፈናቀሉ ሰዎች ቁጥር “አሁንም ከሚገመት በላይ ከፍተኛ ነው” ብሏል።

የመንግስታቱ ድርጅት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽነር ፊሊፖ ግራንዲ “አሁን የምንኖረው በአለም አቀፍ ግንኙነቶች ውስጥ ከፍተኛ ተለዋዋጭነት ባለበት ወቅት ላይ ነው፣ ዘመናዊ ጦርነት ደካማ እና አሰቃቂ በሆነ የሰው ልጅ ስቃይ የተሞላ መልክዓ ምድር እየፈጠረ ነው። ብሏል።

ወቅታዊ መረጃዎች እንደሚያሳዩት ሱዳን በተፈናቃዮች ቁጥር ሶርያን በልጣለች።

በግንቦት ወር አጋማሽ ከአሳድ ስርዓት ውድቀት ወዲህ ከ500,000 በላይ ሶሪያውያን ወደ አገራቸው የተመለሱ ሲሆን1.2 ሚሊዮን የሚገመቱ ተፈናቃዮች ደግሞ ከህዳር ወር መጨረሻ ጀምሮ ወደቀያቸው ተመልሰዋል።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን እንዳለው በ 2025 መጨረሻ እስከ 1.5 ሚሊዮን ሶርያውያን ተፈናቃዮች ሊመለሱ እንደሚችሉ ይገምታል።

በአሁኑ ወቅት ሱዳን 14.3 ሚሊዮን ስደተኞች እና ተፈናቃዮች በማስመዝገብ ከዓለም ቀዳሚ ስትሆን፣ ሶሪያን (13.5 ሚሊዮን)፣ አፍጋኒስታን (10.3 ሚሊዮን)፣ ዩክሬን (8.8 ሚሊዮን) ስደተኞች በማስመዝገብ በዓለም በቀደም ተከተል ተቀምጧል።
ስደትን፣ ግጭትን፣ ብጥብጥን፣ የሰብአዊ መብት ረገጣን እና የህዝብን ጸጥታ በከፍተኛ ደረጃ የሚያውኩ ሁነቶችን ለመሸሽ የተገደዱ ሰዎች ቁጥር ባለፉት አስርት አመታት በእጥፍ ጨምሯል።

ባለፈው አመት መጨረሻ ላይ በአለም አቀፍ ደረጃ የ123.2 ሚሊዮን ቸፈናቃዮች አሃዝ ከ2023 መጨረሻ ጋር ሲነጻጸር በሰባት ሚሊዮን ከፍ ብሏል።

“በአለም አቀፍ ደረጃ ከ67 ሰዎች አንዱ በ2024 መጨረሻ ላይ በግዳጅ ተፈናቅሏል” ሲል ኮሚሽኑ አስታውቆል።

በአጠቃላይ 9.8 ሚሊዮን በግዳጅ የተፈናቀሉ ዜጎች በ2024 ወደ አገራቸው እንደተመለሱ ሪፖርቱ አመልክቷል።

በአሁን ጊዜ ሁለት ሶስተኛው ስደተኞች በጎረቤት ሀገራት እንደሚኖሩ የጠቆመው ሪፖርቱ በኢራን (3.5 ሚሊዮን)፣ ቱርክ (2.9 ሚሊዮን)፣ ኮሎምቢያ (2.8 ሚሊዮን)፣ ጀርመን (2.7 ሚሊዮን) እና ዩጋንዳ (1.8 ሚሊዮን) ከፍተኛውን የስደተኞች ቁጥር  የሚያስተናግዱ አገሮች ናቸው።

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates