
ኢትዮ ሞኒተር: 04/10/2017: የተባበሩት ዓረብ ኢሚሬትስ ‘ጥቃትን እየደገፈች ነው’ ስትልም ወቅሳለች።
የሱዳን መንግስት የሊቢያን ወታደራዊ አዛዥ ካሊፋ ሃፍታርን የፈጣን ድጋፍ ሃይል አባል በመሆን ድንበር ዘለል ጥቃት ፈፅሟል በማለት ነው የከሰሰው።
የሱዳን ጦር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በተናጥል በሰጡት መግለጫ በሱዳን፣ ሊቢያ እና ግብፅ መካከል ያለው የሶስት መአዝን ድንበር ለመያዝ የተቀናጀ ጥቃት ነው ሲሉ ኮንነዋል። ጦሩ የ RSF ተዋጊዎች “በካሊፋ ሃፍታር የሊቢያ ጦር እየተደገፉ” “አካባቢውን ለመንጠቅ ሞክረዋል” ይላል መግለጫው። የሊቢያ አንጃ ተሳትፎ “ከዚህ በፊት ታይቶ የማይታወቅ” የአለም አቀፍ ህግ ጥሰት እና ክልላዊ ሴራ” በማለት ጠርቶታል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ድርጊቱን “አደገኛ ትንኮሳ” ብሎ የጠራው ሲሆን “በአቡ ዳቢ አገዛዝ” የተደገፈ ነው ብሏል። ከሊቢያ ጋር ያለው ድንበር “የጦር መሳሪያዎች እና ቅጥረኞች ዋና መሻገሪያ ሆኗል የሚለው መግለጫው በተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ የገንዘብ ድጋፍ እና የሃፍታር ሃይሎች ቅንጅት” ፈጥሯል ብሏል። በተጨማሪም “የፀጥታው ምክር ቤት እና የምዕራባውያን ኃይሎች ገርነት” ሲል የገለጸውን በጦርነቱ ውስጥ ተጨማሪ ክልላዊ ተሳትፎን አበረታቷል ሲል ተችቷል።
ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በተለይም የተባበሩት መንግስታት ድርጅት፣ የአፍሪካ ህብረት እና የአረብ መንግስታት ሊግ ይህንን ጥቃት እንዲያወግዙ እና ለሱዳን ሉዓላዊነት፣ አንድነት፣ ቀጣናዊ ደህንነት እና መረጋጋት ምላሽ እንዲሰጡ እንጠይቃለን ብሏል የሱዳን ውጭ ጉዳይ ሚ/ር መግለጫ።