
ኢትዮ ሞኒተር: 04/10/2017: ዛሬ በመቐለ ከተማ ሰላማዊ ሰልፍ እያደረጉ ያሉት የምዕራብ ትግራይ የተፈናቃዮች ከጊዝያዊ አስተዳደሩ የሚሰማቸው ባለ ስልጣን ስያጡ ጥበቃዎችን ገፍትሮ መግባታቸው ታውቋል።
“በኬንዳ ለአምስተኛው ክረምት አንከርምም” የሚል መፈክር ስያስተጋቡ የተሰሙት ተፈናቃዮች ዛሬ ግንቦት 4 ቀን 2017 ዓ/ም ባካሄዱት ሰልፍ ወደቀያቸው እንዲመለሱ ተማፅኗል።
ተፈናቃዮቹ በትግራይ በደረሰው አስከፊ ጦርነት ከመኖሪያ ቤታቸው ተፈናቅለው አራት ክረምት በኬንዳ አሳልፈዋል።
ተፈናቃዮቹ ከአራት ዓመታት በላይ በአሮጌው ኬንዳ ውስጥ ብርድ እና ንፋስ; ፀሃይና ዝናብ እየተፈራረቀባቸው የሚገኙ እና በምግብና መድኃኒት እጦት በርካቶች ለሞትና ለበሽታ መዳረጋቸውን ይናገራሉ።
በዚህም በኬንዳ ለአምስተኛ ክረምት እንዳያሳልፉ ለመጠየቅ ሰልፉን ለማካሄድ ተገደዋል።
ሰላማዊ ሰልፉ በዋናነት ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ድምፃቸውን ለማሰማት ያለመ ሲሆን ከክረምት በፊት ወደ ቤታቸው እንዲመለሱ ለማድረግ ነው።
ተፈናቃዮቹ የፌደራል መንግስት፣ ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) እና የፕሪቶሪያ ውል አደራዳሪዎችን ጥያቄያቸውን ሊመልሱላቸው እንደሚገባ ጥሪ አቅርቧል።
“የግዛት አንድነታችን ይመለስ፡ በኬንዳ ለአምስተኛው ክረምት አንቆይም፤ ፍትህ ለተፈናቃዮቹ እና ለሌሎችም መፈክሮች በመያዝ ድምፃቸው አሰምቷል።
እየኖሩ ያለውን አስከፊ ህይወት ለማሳየት የተለያዩ የቤት ቁሳቁሶችን ይዘው ወጥቷል።
“ፅላል” የተሰኘው የምዕራብ ትግራይ ሲቪል ማህበረሰብ ከሰኔ 11-13 ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ እንደሚያካሂድ አስታወቋል።
ሰላማዊ ሰልፉ በመቀሌ እና በጄኔቫ እንደሚካሄድ ታውቋል።