ማህበራዊፖለቲካ

በትግራይ ያለው የፖለቲካ ሁኔታ አጥፊ ነው” ሲሉ የትግራይ ጊዝያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ሌተና ጄኔራል ታደሰ ወረደ ተናገሩ

ኢትዮ ሞኒተር፡ 03/10/17፡ “በትግራይ ያለው የፖለቲካ ሁኔታ አጥፊ ነው” ሲሉ የትግራይ ጊዝያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ሌተና ጄኔራል ታደሰ ወረደ ተናገሩ፡፡ በትግራይ ክልል በትላንትናው እለት የሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ የተከናወነ ሲሆን በዚህ መድረክ ላይ የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝደንት ሌተና ጄኔራል ታደሰ ወረደ ንግግር አድርገዋል፡፡

በንግግራቸውም ‹‹በትግራይ አሁን ያለው የፖለቲካ ሁኔታ አጥፊ ነው፡፡ ይህ ጥፋት እንዳይከሰት የመከላከል ስራ መስራት አለብን›› ያሉት ፕሬዝደንቱ ጨምረውም ‹‹ፖለቲከኞች የፈጠሩት ችግር የትግራይ ዋና ጉዳይ እንዲረሳ አድርጎታል፡፡ ሁሉም አካላት የትግራይን ችግር በሀይል መፍታት እንደማይቻል ሊረዱት ይገባል›› በማለት መልእክት አስተላልፈዋል፡፡

ሲቀጥሉም ‹‹በአሁኑ ወቅት በትግራይ ያለውን አደጋ ማሸነፍ የሚቻለው በሰላማዊ መንገድ፣ በአንድነትና በመግባባት ነው›› ብለዋል፡፡ በዛሬው ጉባኤ ላይ ከስምንት የሀይማኖት ተቋማት የተውጣጡ 110 የሀይማኖት አባቶችና የፅህፈት ቤት ሀላፊዎች መገኘታቸው ተገልጿል፡፡

በዚህ ጉባኤ ላይ ‹‹የሀይማኖት አባቶች ለትግራይ ሰላምና አንድነት ያላቸው ሚና›› በሚል ርእስ ጥናታዊ ፅሁፍ ያቀረቡት አቶ ካልአዩ በ1993 የህወሀትን ክፍፍል ጠቅሰው በመሪዎች መካከል ያሉ አመመግባባቶች በሰላማዊ መንገድ ካልተፈቱ አደጋው ከባድ መሆኑን ማስረዳቸውን የክልሉ ማስ ሚዲያ ዘግቧል፡፡

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates