Uncategorized
ኢራን የእስራኤል ወታደራዊ መረጃዎች ሰብራ በመግባት ሁሉንም የእስራኤል ወታደራዊ ሚስጥሮች ሞንትፋ መውሰዷ ተረጋግጧል።

ኢትዮ ሞኒተር፡ 03/10/17፡ ኢራን የእስራኤል ወታደራዊ መረጃዎች ሰብራ በመግባት ሁሉንም የእስራኤል ወታደራዊ ሚስጥሮች ሞንትፋ መውሰዷ ተረጋግጧል።
በዚህ መሰረት የእስራኤል የኑክሌያር ጣቢያዎች ፣ የመሳሪያ ማከመቻዎች ፤ የጦር ፕሮግራሞች ፤ የጦር እቅዶችን ፤ ከአውሮፓ እና አሜሪካ ጋር ያላትን ወታደራዊ ትብብር ሁሉ ሰብራ መውሰዷ ታውቋል።
የኢራን የደህንነት መስሪያቤት ዛሬ በሰጠው መግለጫ በሺዎች የሚቆጠሩ የእስራኤል የሳይንስ ወታደራዊና የኑክሌር መረጃዎቿን ሰብረን ወስደናል፤ ከምእራባውያን ጋር ያላትን ግንኙነቶች ሁሉ ሰብረን ወስደናል፤ ይህንን መረጃ ከእስራኤል ወደ ኢራን ለመውሰድ የተጠቀምንበትን መንገድ ይፋ አናደርግም ብሏል። መስሪያቤቱ አክሎም እነዚህ ቁልፍ መረጃዎች ኢራን እስራኤል ላይ ለምታደርጋቸው ማጥቃቶች እጅግ ወሳኝ ናቸው ብሏል።
እስራኤል እስካሁን በጉዳዩ አስተያየት ያልሰጠች ስትሆን በከፍተኛ ሚስጥር ይጠበቃል የሚባለው የእስራኤል ወታደራዊ መረጃ ግን በኢራን መሰበሩ የአለም መገናኛ ብዙሀን ሁሉ መነጋገሪያ ሆኗል